የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ካኪ የአይሱዙ ሞተርስ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ
የካኪ የአይሱዙ ሞተርስ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ የስራ እንቅስቃሴን ጎበኙበት ወቅት አምራች ኢንዱስትሪዎች በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩ ለማስቻል መንግስት አስፈላጊውን ስራ ሁሉ እየሰራ መሆኑን የጠቀሱት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ክቡር አቶ መላኩ አለበል “ሁሉም አምራቾች መዳረሻቸውን ሩቅና ዓለምአቀፋዊ ተወዳዳሪነት ላይ ትኩረት በማድረግ የስራ ውጤታቸው በጥራት፣ በጊዜና በመጠን የተለካ እንዲሆን አድርገው በማቀድ፣ እርስበርስ በመተሳሰር አንዱ ለአንዱ ግብዓት የሚያቀርብበትን ሂደት በመፍጠር የተጠናከረ ትስስራዊ የቅብብሎሽ የስራ ሂደትን በመከተልና ለሚያጋጥማቸው የግብዓት እጥረት መፍትሄ ማበጀት ይጠበቅባቸዋል” ብለዋል፡፡
ሀገራችን የኢንዱስትሪ ጥሬ እቃዎችን ብቻ ሳይሆን እውቀትም በአግባቡ እየገዛች በመሆኑ በዘርፉ የታቀደውን ለውጥ ለማምጣት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መሆናችንን አመላካች ነው ያሉት ሚኒስትሩ በድርጅቱ ውስጥ እየተሰራ ያለው የቴክኖሎጂ ሽግግርና የሰው ሀብት ልማት ስራም አበረታች መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አምራቾች ለቆሙለት ዓለማ ስኬት እውን መሆን፣ ለስራ ዕድል ፈጠራ፣የውጭ ምንዛሬን ማዳንና ሌሎች ወሳኝ የሚባሉ የሀገር ኢኮኖሚ ላይ የዜግነት ድርሻቸውን በመወጣት እንደ ሀገር የተያዘውን የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር በማሳለጥ እምርታዊ ለውጥ ለማስመዝገብ ሰው ሀብት ልማት ላይ አበክረው መስራት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
Leave a Comments